Wednesday, July 13, 2016

ድካማችንንም እንደ ጥንካሬ (ግንቦት 11፣2007 ዓ.ም.)


እውን የጥንካሬ ማሳያ ነውን?

ከመንግስታችን ሚዲያና ከመንግስት   ባለስልጣናት አንደበት በተደጋጋሚ የምሰማው ነገር ይገርመኛል፡፡ ነገሩ እንደዚህ ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመንቀሳቀስ ነዋሪዎቹን ሲያወያዩአቸው በየስፍራው ያለው ህዘብ እዚያም እዝህም የሚታየውን የልማት ጥያቄውን ያነሳል፡፡ በተለይም ደግሞ ሊሰሩ ቃል የተገቡ በርካታ የመንገድ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ የትምህርት ቤቶች ወዘተ አሊያም ስራቸው ተጀምሮ ለረጅም ዓመታት ሳይጠናቀቅ የቆዩ ወይም ተጠናቀው አገልግሎተ መስጠት ሳይጀምሩ ስለቆዩት የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ነዋሪዎች ቅራኔዎቻቸውን ወይም ጥያቄዎቻቸውን በስፋት ያነሳሉ፡፡ እንግዲህ እነዚህና መሰል ጥያቄዎች ሲጎርፉላቸው የመንግስት ባለስልጣናቱ መልስ የሚሰጡበት ጊዜ ሲደርስ ጥያቄዎቹ ለመንግስታቸው ውጤታማነት ጉልህ ማሳያዎች መሆናቸውን ለማሳየት እንዲህ በማለት ይጀምራሉ “መንግስታችን የመልማት ፍላጎት ያለውንና የልማት ጥያቄ ማንሳት የሚችል ህዝብ መፍጠር የቻለ መንግስት ነው”

No comments: